• ልደታ ጎማ ቁጠባ ፖሊስ መመሪያ ጊቢ ዉስጥ
  • +251912689710
  • ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም

የኮሚሽኑ ተግባራትና ኃላፊነት

የፓርቲውን ህይወት መጠበቅ

  • ሀ) የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን መከታተል
  • ለ) የፓርቲውን የፖለቲካ ጥራትና የሥነምግባር ጤናማነት ለማረጋገጥ ክትትል ማድረግ
  • ሐ) የፓርቲ ሥነ ምግባርን ያሻሽላል፣ ሙስናን ለመዋጋት ጥረቶችን ማድረግ፣ ማስተባበር
  • መ) የሥነ ምግባር ጥሰቶችን መመርመር፣ ተገቢውን የእርምት ርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ
  • ሠ) ከፓርቲው አስተባባሪ ኮሚቴዎች በሚሰጥ ተልእኮ ምርመራ፣ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ
  • ረ) በፓርቲው አካላት መካከል ልዩነት ሲኖር ወይም መጣራት የሚገባቸው ጉዳዮች ሲኖሩ እንዲሁም በፓርቲው ማ.ኮ/ሥአኮሲጠየቅ አጣርቶ የውሳኔ ሀሳብ ሪፖርት ለማ/ኮሚቴ ያቀርባል

የፓርቲውን አባላት መብት መጠበቅ

  • ሀ) የፓርቲው አባላትና አካላት መብቶች እና ጥቅሞች መከበራቸውን ይከታተላል

  • ለ) ከአባላት የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ይቀበላል፣ ይመረምራል፣ የእርምት የውሳኔ ሐሳቡን ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና እንደ አግባቡ በየደረጃው ላሉ የፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ያቀርባል

  • ሐ) ፓርቲው ርምጃ የተወሰደበት አባል/ዕጩ አቤቱታውን በየደረጃው ላለው የፓርቲ መዋቅር አቅርቦ ካልረካ በየደረጃው ላለው ኮሚሽን ሊያቀርብ ይችላል

የኮሚሽኑ የውስጥ አሠራሮች

  • ሀ) ዝርዝር የሥነ ምግባር፣ የኢንስፔክሽንና የቁጥጥር መመሪያ በማርቀቅ ለፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አቅርቦ ያጸድቃል፣ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል
  • ለ) ኢንስፔክሽንና ልዩ ልዩ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ የጥናቱን ግኝቶች ከውሳኔ ምክረ ሐሳብ ጋር ለሚመለከታቸው የፓርቲ አካላት ያቀርባል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል
  • ሐ) ለሥራ የሚያስፈልገውን ዓመታዊ በጀት በማዘጋጀት እንዲፀድቅ ለማዕከላዊ ኮሚቴ ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ያስተዳድራል፣ ይመራል፤
  • መ) ለፓርቲው ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ተገዢ ያልሆኑ የኮሚሽኑ አባላትን በ2/3ኛ ድምጽ ያግዳል
  • ሠ) ስለሥራው ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ያቀርባል
  • ረ) የኮሚሽኑን የውስጥ የአሰራር መመሪያዎች ማውጣት ይችላል