የልደታ ክ/ከተማ የእንስፔክሽን እና ስነ ምግባር ኮሚሽን ኃላፊ መልእክት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ለአመራሮች ፣ ለባለሙያዎች እና ለሰራተኞች እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዋና አላማዉም በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት የሚያደርገው ሪፎርም ሙያዊ ስነ ምግባርን የተላበሰ ብቃት ያለውና ለደንበኞች በቂ አክብሮት የሚሰጥ ሲቪል ሰርቫንት መገንባት ነዉ፡፡ በመሆኑም የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርምን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት የክፍለ ከተማውን ሠራተኞች በሁሉም መስክ ለማብቃት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማስጠበቅ ፣ አሰራሮችን ለማሻሻል ፣ የስራ ተነሳሽነት እና ትጋት ያለው የሰው ለኃይል ለመገንባት እንዲሁም ቴክኖሎጂ መር አገልግሎቶችን በመስጠት የተገልጋዩን ጊዜ፣ ገንዘብ ፣ እንግልት እና መሰል ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ይረዳ ዘንድ ይህ የመረጃ ማግኛ እና የእራስን ብቃት መመዘኛ ገጽ በክ/ከተማዉ ጽ/ቤት ቀርቦላችዋል፡፡

አቶ አብረሀም ገረሱ

የልደታ ክ/ከተማ የእንስፔክሽን እና ስነ ምግባር ኮሚሽን ኃላፊ

ጥያቄዎች

ዉድ የክፍለ ከተማችን ሠራተኞች የአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ሙያዊ ስነ ምግባር ፣ ተቋማዊ ግንባታ ፣ የደንበኞች አያያዝ ፣ አመራር እና መሰል ጥያቄዎች በኦንላይን የቀረበላችሁ ሲሆን እራሳችሁንም ትገመግሙ ዘንድ መልሱም ተያይዞላችኋል፡፡

ዶክመንቶች

የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማስጠበቅ ፣ አሰራሮችን ለማሻሻል ፣ የስራ ተነሳሽነት እና ትጋትን ከፍ በማድረግ የተገልጋዩን ጊዜ፣ ገንዘብ ፣ እንግልት እና መሰል ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚረዳዎትን ልዩ ልዩ መረጃዎች ያዉርዱ ያንብቡ ....

ይደዉሉ !

ከደንበኞች አያያዝ ፣ ተቋማዊ ባህል ግንባታ ፣ አገልግሎት አሰጣጥ ፣ ሙያዊ ስነ ምግባር ፣ ተቋማዊ ባህል ግንባታ ፣ አመራር እና መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መረጃ ለመስጠትም ሆነ አጋዥ ዶክመንቶችን ለማጋራት ከፈለጉ እባክዎ ለመደወል አያመንቱ፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ

Feel free to contact us and we will get back to you ass sson as we can.

Let's Get in Touch

  • አድራሻ :

    ጎማ ቁጠባ ከጤና ሚኒስቴር አጠገብ

  • ስልክ ቁ. :

    +2521912689710

  • ኢሜይል :

    info@lidetapp.org

  • ስራ ሰዓት :

    ከሰኞ - አርብ: 2:30 - 11:30
    ቅዳሜ - እሁድ: ዝግ ነዉ፡፡