• ልደታ ጎማ ቁጠባ ፖሊስ መመሪያ ጊቢ ዉስጥ
  • +251919157113
  • ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም

image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ስነ ምግባር ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ከልደታ ክፍለ ከተማ ከእንስፔክሽንና ሥነ ምግባር ጋር የትብብር ስራዎች ስምምነት ማድረጉን አስታወቀ።

መጋቢት 24, 2017
ስምምነቱ በዋናነነት የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ በጥናት ላይ የተመሠረተ ሙስና መከላከል፣ በትውልድ ስነ ምግባር ግንባታ ሙስናን በመከላከል ተጠያቂነት በማስፈን በጋራ መስራት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። የልደታ ክፍለ ከተማ ኢንስፔክሽን እና ሥነ-ምግባር ሰብሳቢ አቶ አህመድ እንድሪስ ፓርቲ እያከናወንናቸው ለሚገኙ የስነ ምግባርና ኢንስፔክሽን ስራዎች አጋዥ የሚሆን ስምምነት መሆኑን ገልፀዋል። አያይዘውም ውጤታማ የሆኑ ስራዎችን ለመስራት ብሎም የፓርቲው ሀብቶች በአግባቡ መጠበቃቸውን መከታተል እና መሰል ተግባራት ላይ ለምንሰራቸው ስራዎች ስምምነቱ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል። የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ባለሙያ አቶ መላኩ ጌታሁን የስምምነት ሰነዱን በውስጡ የያዛቸውን ዋና ዋና ተግባራት የሚገልፅ ሰነድ በመድረኩ አቅርበው በሁለቱም ተቋም የስምምነት ፊርማ ተፈርሟል። "ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!”

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች