በልደታ ክ/ከተማ "የፀረ ሌብነት ትግሉና የአመራሩ ሚና " በሚል መሪ ቃል ለክፍለ ከተማና ለወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ስልጠና ተሰቷል።
የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሓፍቱ ብርሀኑ በስልጠናው ወቅት እንደተናገሩት ማህበረሰቡ ኃላፊነት የሰጠን ልማትና መልካም አስተዳደርን አስፍነን ፍትሀዊ ተጠቃሚነቱን እንድናረጋግጥለት እንጅ ሌብነትና በብልሹ አሰራር ን ሳንታገል የህብረተሰባችንን ጥቅም እንድናሳጣው አይደለም ስለዚህ ከማህበረሰባችን ጋር ሆነን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጠንቅ የሆነውን ሌብነትና ብል አሰራርን መታገል ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል።
አቶ ሓፍቱ አክለውም ሌብነትን በመታገል ረገድ አመራሩ የመሪነት ሚናውን መወጣት ይኖርበታል ያሉ ሲሆን የፓርቲያችን ቀይ መስመር የሆነውንም ሌብነትን አምርረን በመታገል ለውጥ ማምጣት ይኖርብናል በማለት ገልፀዋል።
አመራር ላይ የተቀመጥነው የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ እስከሆነ ድረስ ሌባን ሌባ እያልን በህግ- እየጠየቅን እንሄዳለን ያሉት አቶ ሓፍቱ በአንድ በኩል ሌብነትን እየታገልን በሌላ በኩል ፍትሀዊ የሆነ ልማትን እያረጋገጥን የክ/ከተማችን ብልፅግና እናረጋግጣለን ሲሉ ገልፀዋል።
ለህዝብ ጥቅም የሚተጉትን እንጅ የአሰራር ጥሰት በመፈፀም የመንግስትን ሀላፊነት ለሀብት ማካበቻነት የሚጠቀሙ አመራሮችን አንታገስም ያሉት አቶ ሓፍቱ ሌብነትን በመከላከል ሂደት ማህበረሰቡ ከጎናችን ሆኖ ሊሰራ ይገባል በማለት ተናግረዋል።
ስልጠናውን የሰጡት የብልፅግና ኢንስፔክሽን ስነ-መግባር ኮሚሽን ዋና ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ነስረዲን መሀመድ እንደተናገሩት በፓርቲ ጉባኤ የተሻሻሉ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ለፓርቲው ተቋማዊ ስኬት የድርሻቸውን አበርክቶ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ኢንስፔክሽን እና ስነ-መግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሀም ገረሱ ስልጠናው አመራሩ ለሚያከናውናቸው ተግባራት ምቹ መደላድል ይፈጥራል ብለዋል።
በእለቱም በተሻሻለው የፓርቲ መተዳደሪያ እና የኮሚሽን መመሪያ ዙሪያም ስልጠና ተሰጥቷል።
መልዕክትዎን ይላኩ