• ልደታ ጎማ ቁጠባ ፖሊስ መመሪያ ጊቢ ዉስጥ
  • +251919157113
  • ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም

image
image
image
image
image

ሙስና የማይሸከም ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም ዜጋ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

ሰኔ 2, 2017
በመድረኩ " የሙስና ፅንሰ ሀሳብ እና የመከላከያ ስልቶች " በሚል የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የልደታ ክፍለ ከተማ ኢንስፔክሽንና ሥነ ምግባር ኮሚሽን ቅርጫፍ እና የክፍለ ከተማው የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ጋራ በመሆን ብልሹ አሰራርን በመከላከልና መልካም አስተዳደርን ለማስረፅ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል። የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ሥነ ምግባር ኮሚሽን ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኮሚሽነር አቶ አብርሃም ገረሱ ሙስናን የማይሸከም ትውልድ መፍጠር ያስፈልጋል በማለት ይህ እንዲሳካ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና በቁርጠኝነት መወጣት ይኖርበታል በማለት ገልፀዋል። ሙስናን ለመቅረፍ በሚያስችል አግባብ የአደረጃጀቶችን ተሳትፎ በማዳበር የማህበረሰብን አቅም በስፋት መጠቀም ይገባል ያሉት አቶ አብርሀም ተግባራትን በጋራ በመስራት የሚያጋጥሙንን ችግሮች መቅረፍ እንዲቻል ሁሉም አደረጃጀት የራሱን ሚና በባለቤትነት እና ቁርጠኝነት መወጣት ይገባል በማለት ገልፀዋል። በውይይት መድረኩም ተሳታፊዎች እደገለፁት ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው በሙስና ዙሪያ ማህበረሰብን በማስገንዘብ ረገድ እየተሠራ ያለውን ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች