- ልደታ ጎማ ቁጠባ ፖሊስ መመሪያ ጊቢ ዉስጥ
-
+251919157113
የኮሚሽኑ ተግባራትና ኃላፊነት
የፓርቲውን ህይወት መጠበቅ
- ሀ) የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን መከታተል
- ለ) የፓርቲውን የፖለቲካ ጥራትና የሥነምግባር ጤናማነት ለማረጋገጥ ክትትል ማድረግ
- ሐ) የፓርቲ ሥነ ምግባርን ያሻሽላል፣ ሙስናን ለመዋጋት ጥረቶችን ማድረግ፣ ማስተባበር
- መ) የሥነ ምግባር ጥሰቶችን መመርመር፣ ተገቢውን የእርምት ርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ
- ሠ) ከፓርቲው አስተባባሪ ኮሚቴዎች በሚሰጥ ተልእኮ ምርመራ፣ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ
- ረ) በፓርቲው አካላት መካከል ልዩነት ሲኖር ወይም መጣራት የሚገባቸው ጉዳዮች ሲኖሩ እንዲሁም በፓርቲው ማ.ኮ/ሥአኮሲጠየቅ አጣርቶ የውሳኔ ሀሳብ ሪፖርት ለማ/ኮሚቴ ያቀርባል
የፓርቲውን አባላት መብት መጠበቅ
- ሀ) የፓርቲው አባላትና አካላት መብቶች እና ጥቅሞች መከበራቸውን ይከታተላል
- ለ) ከአባላት የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ይቀበላል፣ ይመረምራል፣ የእርምት የውሳኔ ሐሳቡን ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና እንደ አግባቡ በየደረጃው ላሉ የፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ያቀርባል
- ሐ) ፓርቲው ርምጃ የተወሰደበት አባል/ዕጩ አቤቱታውን በየደረጃው ላለው የፓርቲ መዋቅር አቅርቦ ካልረካ በየደረጃው ላለው ኮሚሽን ሊያቀርብ ይችላል
የኮሚሽኑ የውስጥ አሠራሮች
- ሀ) ዝርዝር የሥነ ምግባር፣ የኢንስፔክሽንና የቁጥጥር መመሪያ በማርቀቅ ለፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አቅርቦ ያጸድቃል፣ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል
- ለ) ኢንስፔክሽንና ልዩ ልዩ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ የጥናቱን ግኝቶች ከውሳኔ ምክረ ሐሳብ ጋር ለሚመለከታቸው የፓርቲ አካላት ያቀርባል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል
- ሐ) ለሥራ የሚያስፈልገውን ዓመታዊ በጀት በማዘጋጀት እንዲፀድቅ ለማዕከላዊ ኮሚቴ ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ያስተዳድራል፣ ይመራል፤
- መ) ለፓርቲው ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ተገዢ ያልሆኑ የኮሚሽኑ አባላትን በ2/3ኛ ድምጽ ያግዳል
- ሠ) ስለሥራው ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ያቀርባል
- ረ) የኮሚሽኑን የውስጥ የአሰራር መመሪያዎች ማውጣት ይችላል
የኮሚሽኑ አመራሮች
አብረሀም ገረሱ
የልደታ ብልፅግና ኢንስፔክሽን እና ስነምግባር ኮሚሽን ኃላፊ
የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ
አልማዝ ተክለህይወት
የልደታ ብልፅግና ኢንስፔክሽን እና ስነምግባር ኮሚሽን ዘርፍ ኃላፊ
የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ